Saturday, January 25, 2014

Geez Bet | 5:27 AM | |
Mogadishu: Somalia's Shebab insurgents called on Saturday for renewed attacks against foreign forces, after arch-enemy Ethiopia joined the African Union force battling the insurgents.
Top commanders of the Al Qaeda-linked group, including insurgent supremo Ahmed Abdi Godane, met this week after Ethiopia formally joined the UN-backed mission known as AMISOM, Shebab spokesman Ali Mohamud Rage said.
"They have declared that the Somali people must intensify their war against AMISOM," Rage said.

“አንድነት” የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ጠየቀ

Geez Bet | 4:43 AM | | |
በግል መጽሄቶች ላይ የቀረበውን ጥናት ተቃውሟል
መንግስት የኢትዮ- ሱዳን ድንበር ጉዳይን ለህዝብ ግልፅ እንዲያደርግ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አና ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በጻፈው ደብደቤ መጠየቁን አስታውቆ፣ በጉዳዩ ላይ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ለመወያየት ቀጠሮ መያዙን ገለጸ፡፡ ፓርቲው በሰጠው መግለጫ፣ ሰሞኑን በሚዲያዎች አጀንዳ ሆኖ የሰነበተውን የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማሻሻል ጉዳይ በጥልቅ እየከታተለው መሆኑን አመልክቶ፣ ህዝቡ የድንበር ማካለል ሂደቱን ጉዳይ የማወቅ መብት እንዳለው መንግስት ተገንዝቦ ጉዳዩን ይፋ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡
መንግስት በሉአላዊነት ጉዳይ ላይ ብቻውን የመወሰን መብት የለውም ያሉት የፖርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ በደፈናው በድንበር ጉዳይ ስምምነት ላይ ተደርሷል የሚል መግለጫ መሠጠቱ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ፓርቲያቸው ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ለመወያየት ለጥር 18 ቀን 2006 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

Powered by Blogger | © Copyright 2014 www.geezbet.com | Designed By Geez Bet = If you need such type blog, call on 09 1919 3131